ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በርቀት ትምህርት መርሃ-ግብር በ2009 ዓ.ም
- በ Accounting & Finance
- በ Economics
- በ Management
- በ Agri-Economics & Agribusiness Management
- በ Rural Development & Agricultural Extension
- በ Natural Resource Management እና
- በ Horticulture
የትምህርት ዘርፎች በቅድመ ምረቃ(ዲግሪ) መርሃ-ግብርተማዎችን ተቀብሎ ማሰተማር ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ማንኛውም አመልካች እስከ የካቲት 5 ቀን 2009 ዓ.ም በሥራ ሰዓት በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ ግቢ የርቀት ትምህርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርቦ ማመልከት የሚችል መሆኑን በደስታ እንገልጻለን፡፡
አመልካቾች፡-
- የቀድሞ 12 ኛ ወይም የ10ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ዉጤት እንግሊዘኛ እና ሂሳብን ጨምሮ 2.00 ነጥብና ከዚያ በላይ ያላት/ያለዉ:: በተጨማሪም ዕዉቅና ካለው ዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ ዲፕሎማና Level 4 የብቃት ማረጋገጫ ፈተና / COC/ ያለፈ/ች፡፡ ከዚያም በላይ ያላት/ያለዉ፡፡
- የመሰናዶ ትምርት ላጠናቃቁ አመልካቾች በየዓመቱ ት/ት ሚኒስቴር ባወጣው በተከታታይና ርቀት ት/ት የከፍተኛ ት/ት መግቢያ ዉጤት መሰረት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ሁሉም አመልካቾች ዋናውን የትምህርት ማስረጃ ከማይመለስ ሁለት ፎቶኪፒ ና ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ጋር ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል
- የማመልከቻፎርሙን ከርቀት ትምህርት ማስተባበሪያ ቢሮ ወይም ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዌብሳይት (www.haramaya.edu.et/college of continuing and distance education )ላይ ማግኘት የምትችሉ ማሆኑን እንገልጻለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፡-0255530372/0255530096 ደውለዉ ይጠይቁን።
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ እና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት