Quantcast
Channel: Haramaya University
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1085

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እየሰጠ ያለው የነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት የአካባቢውን የማህበረሰብ ጥያቄ ከመመለስ ባሻገር በፍ/ቤቶች አየተሰጠ ያለውን የፍርድ ህደት ቀልጣፋ በማድረግ ጉልህ አስተዋፆ በማበርከት ላይ መሆኑ ተገለፀ።

$
0
0

በሸምሸዲን መሐመድ/ከህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ለእድገት መሠረት እንጥላለን በሚል መሪ ቃል ላለፉት ስድስት አስርት አመታት በመማር ማስተማር፤ በምርምርና ስርፀት እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች ከማህበረሰቡና ከተለያዩ አጋርና ባለድርሻ አካላቶች ጋር በመሆን ለአገራችን እድገት የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላያ ያለው የሐረማያ ዪኒቨርሲቲ እንደማንኛዉም የአገሪቱ የከፍተኛ ት/ት ተቋም ማህበረሰቡን ያሳተፈ አገልግሎት የመስጠት ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

ፕ/ር ከበደ ወ/ፃዲቅ የሐረማያ ዪኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተሳትፎ ልማትና ኢንተርፕራይዝ ም/ፕሬዝዳንት ዩኒቨርሲቲው ከመማ ርማስተማር ስራው ጎን ለጎን የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ስራዎች እየሰራ መሆኑንና  በፍትህ ዘርፍም በዩኒቨርሲቲው ህግ ኮሌጅ እየተሰጠ ያለው ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ለፍትህ ተደራሽነት ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገ መሆኑን ሰሞኑንከተለያዩየሚዲያተቋማትለተውጣጡጋዜጠኞችበጽ/ቤታቸውበሰጡትጋዜጣዊመግለጫገልፀዋል።

1

ዩኒቨርሲቲው በሚሰጠው ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ሴቶችና ህጻናት፣አቅመ ደካማና አካል ጉዳተኞች፣ የህግታራሚዎች፣ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ዜጎችና ሌሎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲው የህግ ኮሌጅ የማህበራዊ ፍትህ ሃላፊ አቶ ሱልጣን ቃሲም በበኩላቸው እንደገለጹትዩኒቨርሲውከሐምሌ 1 ቀን 2005 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2008 ዓ.ም ብቻ በቃል ምክር አገልግሎት፣ ክስና ይግባኝ በመጻፍ አገልግሎት ፣ በውክልና ፍ/ቤት በመቆም እንዲሁም የታራሚዎች ጉዳይ በመከታተል አገልግሎትና የህግ ግንዛቤ ትምህርት በመስጠት በአጠቃላይ ለ336,314 ዜጎችነጻየህግድጋፍአገልግሎትመሰጠቱንና ይህም አገልግሎት በትንሹ  በአማካይ በገበያ ዋጋ ሲተመን 80,660,150ብር እንደሆነ ገልፀው በአሁኑ ወቅትም አገልግሎቱ በ43 የህግ ድጋፍ መስጫ ማዕከላት እየተሰጠ መሆኑንአስረድተዋል።

2

አቶሱልጣንቃሲም አክለውም ነጻየህግድጋፍካገኙትመካከልም 80 በመቶውያህሉየፍትህአገልግሎትተጠቃሚማድረግመቻሉንገልጸዋል።

የጋዜጠኞች ቡድኑ ስለአገልግሎቱ አሰጣጥና ተደራሽነት ለአንድ ሣምንት በሐረሪ ክልል፣በኦሮሚያ ክልል በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖችና ወረዳ ፍ/ቤቶች ባደረገው ምልከታ የሐረማያወረዳአዴሌ ወልተሃ ቀበሌገበሬማህበርነዋሪ የሆኑትአቶዑመር ኢብሮ በርከሌ፣ የኮምቦልቻ ወረዳ የቀቀሊ ቀበሌገበሬማህበርነዋሪ ወ/ሮ ዘቢዳ ኢብራሂም፣ በሐረሪ ክልል የሐረር ከተማ ቀላድ አምባ ነዋሪ የሆኑት ተማሪ አላዛር ገነትና አቶ ደረስ አይቼህዩኒቨርሲቲውበአካባቢያቸውወንጀልእንዳይስፋፋና መልካምአስተዳደርእንዲሰፍን በሚያደርገው የነጻየህግድጋፍአገልግሎት ተጠዋሚ መሆናቸውን ገልጠው በተሰጣቸው  አገልግሎት ተገቢውን ፍትህ ማግኘታቸውን ለቡድኑ አስረድተዋል ፡፡

3

ዩኒቨርሲቲው የህግ ተደራሽነትን ቀልጣፋና ምቹ በማድረግ ለታራሚዎች የነፃ የህግ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን የተመለከተው የጋዜጠኞች ቡድን በምዕራብ ሐረርጌ በሀብሮ ወረዳ ማረሚያ ቤት በመገኘት ባደረገው ምልከታ ዩኒቨረሲቲው በ2007 ዓ.ም በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ነፃ የህግ አገልግሎት ማዕከል በመክፈት ለታራሚዎቹ በቂ የህግ ግንዛቤ ከማስጨበጥ በተጨማሪ በሀሰት ምስክር ምክኒያት በደረሰባቸው እንግልት ይግባኝ ለመጠየቅ ባለመቻላቸው፣በገንዘብ እጦትና በሌሎች ምክኒያቶች ሊደርስባቸው የሚችለውን ውጣ ውረድ ማስቀረት መቻሉንና በአሁኑ ሰዓትም በየወሩ ከአስር በላይ የሆኑ ታራሚዎች የጥብቅና አገልግሎት፣ከ20 እስከ 25 ለሚሆኑ ታራሚዎች ደግሞ የፁሁፍ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑንና በህገ መንግስቱና በወንጀል ህጉ የተቀመጡትን የታራሚዎችን መብት በማስጠበቅ በተለይም ጠበቃ ማቆም ያልቻሉ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ እስከአሁን ከአስር በላይ ለሚሆኑ በሀሰት ምስክር ለተመሰከረባቸው የህግ ታራሚዎች ዩኒቨርሲቲው የጥብቅና አገልግሎት በነፃ በመስጠቱ በነፃ  መለቀቃቸውን አረጋግጧል፡፡

5

አቶ መሀመድ ሣኒ የሚባል በሀብሮ ወረዳ ገለምሶ ከተማ 01 ቀበሌ ነዋሪ የሆነ ሰው ድብደቦ አካል ጉዳት አድርሷል በሚል በፍታብሔር ተከሶ 465ሺህ ብር እንዲከፍል ተፈርዶበት የነበረ ሲሁን ዩኒቨርሲቲው ባደረገው ክትትል ታራሚው አድርሶታል የተባለው የአካል ጉዳት ትክክል አለመሆኑንና ቀድሞም ግለሰቡ አካል ጉዳተኛ መሆኑን ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በማስረዳት ወደ 2700ብር ዝቅ እንዲደረግለትና በወንጀልም ከ6ዓመት ወደ 2ዓመት ከ6ወር ዝቅ እንዲልለት ስለተደረገለት በየኒቨርሲቲው የነፃ የህግ አገልግሎት በጣም መደሰቱን አስረድተዋል፡፡

በማረሚያ ቤቱ ያሉ ታራሚዎቹም ለጋዘጠኞቹ በሰጡት አስተያየት የተሰጣቸው የህግ ግንዛቤ በእጅጉ እንደጠቀማቸው ጠቅሰው ወደ ህብረተሰቡ ሲወጡ ማህበረሰባቸውን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ቃል ገብተው ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠው የነፃ የህግ አገልግሎት ቀጣይነት እንዲኖረው የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ኢሊያስ ያህያ፣የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ ፈቃዱ፣የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አፍሬም ኃይሌ  እንዲሁም አቶ መንገሻ ነጋሽ የሐረማያ ወረዳ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት እያንዳንዳቸው በሰጡት አስተያየት የሐረማያዩኒቨርሲቲእየሰጠ ያለው ነጻየህግድጋፍአገልግሎትየአካባቢውን የማህበረሰብ ጥያቄ ከመመለስ ባሻገር እየሰጡ ያሉትን  የፍርድ ህደት ቀልጣፋ እያደረገላቸው መሆኑን  ገልፀው  የነፃ ህግ አገልግሎቱ አሰጣጥ ስኬታምና ውጤታማ መሆኑንና ዩኒቨረሲቲው ቀጥሮ እያሰራ ያሉት የህግ ጠበቆች በግል በገንዘብ ተቀጥረው ከሚሰሩት ጠበቆች በተሸለ ጥራት እየሰሩ በመሆኑ የፍ/ቤቱን ሥራ እንዲቃለል ማስቻሉን አስረድተዋል፡፡

6

ወ/ሮ አለምነሽ ከበደ የምስራቅ ሐረርጌ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤትና ወ/ሮ ነኢማ አብዱረህማን የሐረማያ ወረዳ የሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ተወካይ ስለ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የነፃ የህግ ድጋፍ አሰጣጥ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ቀደም ሲል የአካባቢውነዋሪበተለይምሴቶች፣አቅመደካሞችናአካልጉዳተኞችችግራቸውን ለመፍታት ከፍተኛ ችግር መኖሩን ጠቅሰው በተለይ ከሁለት ዓመት ወዲህ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እየሰጠ ባለው የነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አቀመ ደካማ ሴቶች ተገቢውን ፍትህ ማግኘታቸውን አስረድተው አገልግሎቱ ይበልጥ ተደራሽነት እንዲኖረው የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚያበረክቱ ገልፀዋል፡፡

የጋዜጠኞች ቡድኑ ከተለያዩ ተቋማት ማለትም ከአዲስ ዘመን፣ከአዲስ አድማሰ፣ ከአዲስ ስታንዳርድ፣ ከሄራልድ፣ከሪፖርት፣ከበሪሳ  ከኦሮሚያ ቲቪ፣ከሬዲዮ ፋና 94.8 ኤፍ ኤም፣ ከኢዜአ፣ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማበረሰብ ሬዲያ ኤፍ ኤም 91.5 የህግ አገልግሎት ክፍል እና ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የተወጣጡ ናቸው፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1085


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>