Quantcast
Channel: Haramaya University
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1085

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጭሮ አግሮ-አንዱስትሪና መሬት ሀብት ኮሌጅ ወደ የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲነት አደገ

$
0
0

በሸምሸዲን መሐመድ/የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

መንግስት በሁለተኛው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሊሰራቸው ካቀዳቸው አስራ አንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ የሆነውና በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በጭሮ ከተማ ለሚገነባው የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙክታር ከድርና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ህዳር 15 ቀን 2008 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ አስቀምጡ።

1

በሥነ ስርአቱ ላይ አቶ ሙክታር ከዲር እንዳሉት አገሪቷ ለያዘችው የእድገትና ትራንፎርሜሽን ዕቅድ ውጤማነት ለማረጋገጥ ምርምርና ስልጠና ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ መገንባትም በተለይ የአካባቢውን እምቅ የግብርና ሀብት ለመጠቀም በምርምር የታገዘ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ርእሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው መገንባት ለአካባቢው ማህበረሰብ ብሎም ለጭሮ ከተማ እድገት የጎላ መሆኑንም አቶ ሙክታር ገልፀዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንደተናገሩት መንግስት በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዩኒቨርሲቲዎችን በማስፋፋት ብቁና ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል በማፍራት የትምህርት ጥራት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ብለዋል፡፡

በጭሮ ከተማ የሚገነባው የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲም በመማር ማስተማር እና በምርምር ስርፀት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ለማስወገድ የሚያግዝ ባለሙያ በስፋትና በጥራት ለማፍራት የበኩሉን ድርሻ እንደሚያበረክትና በአካባቢው እየተከናወነ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሀብት ወደ ተሻለ እድገት ለማሸጋገር የሚያግዝ መሆኑን አቶ ሽፈራው አመልክተዋል።

የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊይ የሚገነባው ዩኒቨርሲቲ ለማስተማርና ለምርምር ስራ በእውቀት፣በክህሎትና በስነ ምግባር የታነጸ ባለሙያ ለማፍራት ካለው ፋይዳ በተጨማሪ ለከተማዋ እድገት ብሎም ለአካባቢው ህብረተሰብ የተለየ ፋይዳ እንዳለው አስታውቀዋል።

2

የሀገር ሽማግሌዎች የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ እንዲቋቋም የአካባቢው ነዋሪዎች ያቀረቡትን ጥያቄ መንግስት ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረጉ እንዳስደሰታቸው በመግለፅ በዩኒቨርሲቲው ግንባታ ወቀትም አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ሬጅስትራር የነበሩት ዶ/ር ሙክታር አህመድ ዩኒቨርሲቲውን በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ አቶ አሰድ ዚያድ ደግሞ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸው ይፋ ተደርጓል፡፡

3

በስነ ስርአቱ ላይ ክቡር አቶ አዲሱ ለገሠና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናትና ጥሪ የተደረገላቸ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ከድሬደዋና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች በመቀጠል ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የወጣ ሦስተኛው ዩኒቨርሲቲ ሆኗል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1085


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>