የ2012 የትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም የሚከናወን ስለሆነ ከመስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መግባት እንደምትችሉ እያሳወቅን ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎች በቅጣት ምዝገባ የሚካሄደው ትምህርት በሚጀመርበት መስከረም 28 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ብቻ ከመስከረም 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ግቢ ገብተው ምዝገባ መስከረም 11-12/2012 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል፡፡