Quantcast
Channel: Haramaya University
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1085

አስደሳች ዜና ለትምህርት ፈላጊዎች

$
0
0

የሐረማያ ዩንቨርስቲ የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ዳይረክቶሬት በዋናው ግቢ በድሬዳዋ እና በሐረር ካምፓስ በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚንስትሬሽን (MBA) በክረምትና በተከታታይ (ቅዳሜና እሁድ) መርሃ-ግብር ሥልጠና ለመጀመር ዝግጅት አጠናቋል፡፡ ትምህርት የሚሠጠው በዋናው ግቢ በክረምትና ተከታታይ፤ በድሬዳዋና በሐረር ካምፓሶች በተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ይሆናል፡፡

ስለዚህ ምዝገባ በዋናው ግቢ ድህረ-ምረቃ ፕሮግራም አሮጌ አስተዳዳር ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 04 የሚካሄድ በመሆኑ፡- ትምህርት ፈላጊዎች በዲግሪ መርሃ-ግብር በማነጅመንት፣ በአካውንቲንግ እና በኢኮኖሚክስ ትምህርት የጨረሰ/የጨረሰች ሆኖ፡

  1. የመጀመሪያ ዲግሪ ሰርቲፊኬትና ስቱደንት  ኮፒ
  2. ሠራተኛ ከሆነ/ከሆነች ከሚሰሩበት መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ፤
  3.  ከቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም መምህራን የድጋፍ ደብዳቤ በመያዝና በግንባር በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን ፡፡

የክፍያ ሁኔታ በአንድ ክሬዲት ብር 700 (ሰባት መቶ ብር) ሲሆን በተጨማሪም በተርም ብር 500 (አምስት መቶ ብር) የአድሚንስትሪሽን ወጪ ያስከፍላል፡፡

የማመልከቻ ማቅረቢያ ጊዜ፡ ከሰኔ 22/2008 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 04/2008 ዓ.ም ነው፡፡

የመግቢያ ፈተና በሐረማያ ዩንቨርስቲ ዋናው ቅጥር ግቢ ለሁለቱም መርሐ ግብር (የክረምትና ተከታታይ) ሐምሌ 7/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል መማሪያ ክፍል (LTH 11) የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0255530020 እና 0255530391 ዘወትር በስራ ሰዓት መደወል ይቻላል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1085


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>