Quantcast
Channel: Haramaya University
Viewing all 1085 articles
Browse latest View live

ለስድስት የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ፡፡

$
0
0

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ከታህሳስ 28 እስከ ጥር 5 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው ዙሪያ ለሚገኙ ለስድስት የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ለአንድ ሣምንት የህይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ፡፡
በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ጾታ፤ልዩ ፍላጎት እና ኤች አይ ቪ ኤድስ ሜይንስትርሚንግ ዳይሬክቶሬት የኤች አይ ቪ ኤድስ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ይድነቃቸው ተፈራ እንደተናገሩት የስልጠናው ዋና ዓላማ በአሁኑ ጊዜ በሐገር ደረጃ ሰዎች ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ መዘናጋት በመፈጠሩ በበሽታው የመያዝ አጋጣሚ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ስለሆነም በዚህም ወጣቱ የመጀመሪያ ተጋላጭ እንደመሆኑ ኤች አይ ቪ ኤድስ፤ስነ ተዋልዶ እና ጾታዊ ትንኮሳ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲያገኙ ለማስቻል ብሎም በስነ-ተዋልዶ ጤና ችግር በግንዛቤ እጥረት ለከፋ ችግር እንዳይጋላጡ ለተማሪው በቅርበት ያሉት የቀለም መምህራኖቻቸው ስለሆኑ በሚሰጧቸው የምክር አገልግሎት የህይወት ክህሎታቸው እንዲዳብር ለማድረግ ከወዲሁ ለመሰራትና በተለይም ሴት ተማሪዎች ለአላስፈላጊ እርግዝና እንዳይጋለጡና ከዚህም ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አደጋ ላይ እንዳይጥሉ ለማስቻል መሆኑን አስረድተዋል፡፡
1
አቶ ይድነቃቸው አክለውም ስልጠናው በዋነኛነት ከመምህራን የህይወት ክህሎት፤ ስነ ተዋልዶ፤ ጾታዊ ትንኮሳ እና በ ኤች አይ ቪ ኤድሰ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጋር ተያይዞ በግለሰብም ሆነ በሀገር ላይ የሚያሰከትለውን ጉዳት እንዴት መከላከልና መቀነስ እንደሚቻል በተለይ ደግሞ ጾታዊ ትንኮሳን በተመለከተ በት/ቤቶች ውስጥ ችግሩ እንዳይስፋፋና የመምህራን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ መምህራን ያገኙትን እውቀት ወደ ተማሪዎች በማውረድ ለውጥ ለማምጣት ታሰቦ የተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
2
የስልጠናው ተካፋዮችም በበኩላቸው ስልጠናው አቅም እንደፈጠረላቸውና እርስ በእርስም ልምዳቸውን መጋራት እንዲችሉ እድል የፈጠረላቸው መሆኑን ገልፀው ባገኙት እውቀት ተማሪዎቻቸውን ለማንቃት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የድጋፍ ስራም በቀጣይ በገጠር ትምህርት ቤቶች ላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ተካፋይ የሆኑት ከአወዳይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ከሃረማያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ከሃረማያ መሰናዶ ት/ቤት፤ ከሃረማያ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ት/ቤት፤ ከ ዩኒቨርሲቲው ሞዴል ት/ቤት የመጡ 23 መምህራን ናቸው፡፡


የደረቀውን የሀረማያ ሀይቅ ወደ ነበረበት ለመመለስ የህግ ማዕቀፍ ሊኖረው እንደሚገባ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ገለፁ፡፡

$
0
0

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ማዕከል በሀይቁ ተፋሰስ ውስጥ ከሚገኙ ነዋሪዎችና የባለድርሻ አካላት ጋር ሀይቁን ለመመለስ እየተደረገ በሚገኘው ጥረት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡
1
በውይይቱ ላይ ፕ/ር ከበደ ወልደፃዲቅ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎትና ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ባቀረቡት ፅሁፍ ሀይቁን ለመመለስ እንዲቻል በተፋሰሱ ውስጥ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ሕብረተሰቡን በማስተባበር እየተሰራ እንደሚገኝና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችም እየታዩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የአካባቢ ጥበቃ ስራው የአካባቢውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ የንብ ማነብ ፤ የዶሮ እርባታና ተያያዥ ስራዎችን አብሮ በማሰራት የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ ዩኒቨርሲቲው ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
2
ሀይቁን ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ላያ ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ በተደረገው ውይይት ሀይቁ በተወሰነ ደረጃ መመለስ ቢጀምርም ውሀውን ለመስኖ አገልግሎት በመጠቀማቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመልሶ እንዲጠፋ ምክንያት እንደሆነ ፣ የተወሰኑ ሰዎች ደግሞ ቀድሞ የሀይቁ ክፍል የነበረን ቦታ በመውረር ለእርሻ አገልግሎት በማዋላቸው ሀይቁን ዳግም ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ መሆናቸውን ተወያዮቹ ተናግረዋል፡፡ ለመሬት ወረራውና ሌሎቹም ችግሮች ሳይባባሱ በአፋጣኝ መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ተወያዮቹ ጠይቀዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ስለሺ ጌታሁን ሀይቁን በሳይንሳዊ መንገድ መመለስ እንደሚቻል በመረጋገጡ የሀይቁን ደለል ለመከላከል የተጀመረው የአካባቢ ጥበቃ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ መንግስት በቀጣይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራበት ተናግረዋል፡፡
3
ውይይቱን የመሩት የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የሀረማያ ሀይቅ የሀገሪቱን የስነ-ምህዳር ሚዛን ከማስጠበቅ አንፃር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያለው በመሆኑ ተወያዮቹ ያነሷቸውን ችግሮች ቶሎ መፍታት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡ ችግሮቹን በዘላቂነት ለማስወገድ የሀይቁን ወሰን የማካለልና የማስጠበቅ እንዲሁም የውሀውን አጠቃቀም የሚመራበት የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀት እንዳለበት በመጠቆም ወረዳው ጥያቄ አቅርቦ በክልሉ ማፀደቅ ይገባዋል ብለዋል፡፡

FDRE’s President Stresses University should continue on its Community based works

$
0
0

Haramaya University in collaboration with BMVSS, an NGO based in India, donated 300 Jaipur, artificial limb, to individuals residing in eastern Ethiopia.
FDRE President, H.E. Dr. Mulatu Teshome, Indian Ambassador to Ethiopia and Djibouti, Sahri Anurag Shrivastava, Harari Regional State President, H.E. Mr. Murad Abdulhadi and other distinguished guests were in attendance.
1
President Dr. Mulatu addressed the people gathered at the ceremony and said the Ethiopian government is working to ensure the social security/health of the physically disabled, elders and people living in unfavorable conditions to be involved in the growing economic growth of the country and to have a fair representation and coverage in the eyes of the law. He stressed the government together with stakeholders is working to guarantee the wellbeing of these individuals.
2
On a similar note, the President praised the tremendous work the University is doing to support and hire legal representations to people who do not have the means to hire lawyers. The University has 43 legal aid centers in the surrounding areas and serves annually for around 100,000 beneficiaries in these centers. The different donations to schools, health centers and hospitals, and the hard work it does to support the agricultural sector in general are worth mentioning.
The President also appreciated academicians and researchers of the University for their Numerous Projects and their implementations in support of the country’s economic, social and economic situations.
Three individuals who have received the Jaipur donation demonstrated how functional the artificial limb has made their lives and how it made it easy was to carry on with their day-to-day activities.
3
HU’s Office for the Vice-president for Community Development and Enterprise Development gave recognition and presented appreciation gifts to individuals who came from India to facilitate this donation and Prof. R.S. Bansal, who is very instrumental in the whole process and a staff member of College of Veterinary Medicine.
5

4

ለስድስት የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ፡፡

$
0
0

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ከታህሳስ 28 እስከ ጥር 5 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው ዙሪያ ለሚገኙ ለስድስት የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ለአንድ ሣምንት የህይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ፡፡
በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ጾታ፤ልዩ ፍላጎት እና ኤች አይ ቪ ኤድስ ሜይንስትርሚንግ ዳይሬክቶሬት የኤች አይ ቪ ኤድስ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ይድነቃቸው ተፈራ እንደተናገሩት የስልጠናው ዋና ዓላማ በአሁኑ ጊዜ በሐገር ደረጃ ሰዎች ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ መዘናጋት በመፈጠሩ በበሽታው የመያዝ አጋጣሚ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ስለሆነም በዚህም ወጣቱ የመጀመሪያ ተጋላጭ እንደመሆኑ ኤች አይ ቪ ኤድስ፤ስነ ተዋልዶ እና ጾታዊ ትንኮሳ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲያገኙ ለማስቻል ብሎም በስነ-ተዋልዶ ጤና ችግር በግንዛቤ እጥረት ለከፋ ችግር እንዳይጋላጡ ለተማሪው በቅርበት ያሉት የቀለም መምህራኖቻቸው ስለሆኑ በሚሰጧቸው የምክር አገልግሎት የህይወት ክህሎታቸው እንዲዳብር ለማድረግ ከወዲሁ ለመሰራትና በተለይም ሴት ተማሪዎች ለአላስፈላጊ እርግዝና እንዳይጋለጡና ከዚህም ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አደጋ ላይ እንዳይጥሉ ለማስቻል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

s

አቶ ይድነቃቸው አክለውም ስልጠናው በዋነኛነት ከመምህራን የህይወት ክህሎት፤ ስነ ተዋልዶ፤ ጾታዊ ትንኮሳ እና በ ኤች አይ ቪ ኤድሰ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጋር ተያይዞ በግለሰብም ሆነ በሀገር ላይ የሚያሰከትለውን ጉዳት እንዴት መከላከልና መቀነስ እንደሚቻል በተለይ ደግሞ ጾታዊ ትንኮሳን በተመለከተ በት/ቤቶች ውስጥ ችግሩ እንዳይስፋፋና የመምህራን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ መምህራን ያገኙትን እውቀት ወደ ተማሪዎች በማውረድ ለውጥ ለማምጣት ታሰቦ የተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አቶ ይድነቃቸው አክለውም ስልጠናው በዋነኛነት ከመምህራን የህይወት ክህሎት፤ ስነ ተዋልዶ፤ ጾታዊ ትንኮሳ እና በ ኤች አይ ቪ ኤድሰ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጋር ተያይዞ በግለሰብም ሆነ በሀገር ላይ የሚያሰከትለውን ጉዳት እንዴት መከላከልና መቀነስ እንደሚቻል በተለይ ደግሞ ጾታዊ ትንኮሳን በተመለከተ በት/ቤቶች ውስጥ ችግሩ እንዳይስፋፋና የመምህራን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ መምህራን ያገኙትን እውቀት ወደ ተማሪዎች በማውረድ ለውጥ ለማምጣት ታሰቦ የተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡አቶ ይድነቃቸው አክለውም ስልጠናው በዋነኛነት ከመምህራን የህይወት ክህሎት፤ ስነ ተዋልዶ፤ ጾታዊ ትንኮሳ እና በ ኤች አይ ቪ ኤድሰ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጋር ተያይዞ በግለሰብም ሆነ በሀገር ላይ የሚያሰከትለውን ጉዳት እንዴት መከላከልና መቀነስ እንደሚቻል በተለይ ደግሞ ጾታዊ ትንኮሳን በተመለከተ በት/ቤቶች ውስጥ ችግሩ እንዳይስፋፋና የመምህራን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ መምህራን ያገኙትን እውቀት ወደ ተማሪዎች በማውረድ ለውጥ ለማምጣት ታሰቦ የተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

s1

የስልጠናው ተካፋዮችም በበኩላቸው ስልጠናው አቅም እንደፈጠረላቸውና እርስ በእርስም ልምዳቸውን መጋራት እንዲችሉ እድል የፈጠረላቸው መሆኑን ገልፀው ባገኙት እውቀት ተማሪዎቻቸውን ለማንቃት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የድጋፍ ስራም በቀጣይ በገጠር ትምህርት ቤቶች ላይ ተጠናክሮ ጠይቀዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ተካፋይ የሆኑት ከአወዳይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ከሃረማያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ከሃረማያ መሰናዶ ት/ቤት፤ ከሃረማያ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ት/ቤት፤ ከ ዩኒቨርሲቲው ሞዴል ት/ቤት የመጡ 23 መምህራን ናቸው፡፡

 

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጨመዳ ፊኒንሳ ንግግር

$
0
0

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲና ህንድ አገር ከሚገኝ ቢ ኤም ቪ ኤስ ኤስ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች ለሚገኙ 300 አካል ጉዳተኞች የሰው ሰራሽ እግር ተከላና የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የመሰረት ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ምረቃ ላይ የተደረገ ንግግር

ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ  -  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.  ኘሬዚዳንት

የተከበራችሁ የፌዴራልና የክልል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፡-

የተከበራችሁ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ቦርድ አባላት፡-

ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች፡-

ክቡራትና ክቡራን፡-

በቅድሚያ ጥሪያችንን አክብራችሁ ወደ አንጋፋው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንኳን በደህና መጣችሁ ማለት እፈልጋለሁ፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎትና ልማት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካሉአቸው ሶስት ትላልቅ ተልዕኮዎች አንዱ ነው፡፡ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ተልዕኮ በላቀ ለመፈፀም የተሻለ አደረጃጀት በመዘርጋትና የማህበረሰብ አገልግሎትና ልማት ፎኖተ-ካርታ በአሳታፊነት በማዘጋጀት ሰፊ የሥራ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ በፍኖተ-ካርታው መሠረት በተጨባጭ በየዓመቱ በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች፡- በትምህርት፣ በጤና፣ በሥራ ፈጠራና በመሳሰሉት የአቅም ግንባታ ስልጠና ይሰጣል፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ቴክኖሎጂን ያሸጋግራል፤ ያላምዳል፤ በአካባቢው ላሉት ት/ቤቶችና የጤና ተቋማት የቁሳቁስና የተለያዩ ድጋፎችን ያደርጋል፤ በሕይወት ፋና ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት ይሰጣል፤ የተቀናጀ  የሐረማያ ተፋሰስ ልማት ያከናውናል፤ በምሥራቅ ኢትዮጵያ በ43 ማዕከላት ነፃ የሕግ አገልግሎት ይሰጣል፤ የመሠረተ-ልማት ሥራዎች፡- መንገድ፣ የመጠጥ ውሃ፣ የሥራ ቦታዎችንና የመሳሰሉትን እየሰራ ይገኛል፡፡ በቀጣይነትም በዙሪያችን ላሉት ማህበረሰብና ተቋማት ቅድሚያና ልዩ ትኩረት በመስጠት የማህበረሰብ አገልግሎትና ልማት ሥራዎቻችንን አጠናክረን ለመቀጠል አቅደን እየሠራን እንገኛለን፡፡

ክቡር ኘሬዚዳንት፡-

ክቡራትና ክቡራን፡-

ትምህርትን ለሁሉም ዜጐች ተደራሽና የተመቻቸ ለማድረግ እየተደረገ ያለውን ሁለገብ ጥረት ለማሳካት በዩኒቨርሲቲያችን ላሉ 96 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች

ሁኔታዎችን የተመቻቸ ለማድረግ ምቹ የመማሪያ ክፍሎች፣ የመኖሪያ ቤቶች፣ የማንበቢያ ክፍሎች፣ የመፀዳጃ ቤቶች፣ መንገዶችና ቁሳቁሶችን በማሟላት ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ እያደረግን እንገኛለን፡፡ የተለያዩ የትምህርት ድጋፍ፣ የቁሳቁስና በነፍስ ወከፍ በየወሩ ከብር 200 በላይ የፋይናንስ ድጋፎችን እናደርጋለን፡፡ ተመሳሳይ ድጋፎችን ዩኒቨርሲቲያችን አካባቢው ለሚገኙ ሌሎች አካል ጉዳተኞች ተደራሽ ለማድረግ ህንድ አገር ከሚገኘው ቢ.ኤም.ቪ.ኤስ. ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በፈጠርነው ግኑኝነት፣ ማመቻቸትና ድጋፍ ከምሥራቅ ኢትዮጵያ እስከ 300 የአካል ጉዳተኞች ሰው ሰራሽ እግር እንዲሰራላቸው ለማድረግ ተችሏል፡፡ ለዚህ የተቀደሰ ሰብአዊ በጐ ሥራ ቢ.ኤም.ቪ.ኤስ. ድርጅትን፣ እርዳታው እንዲሳካ ያደረጉትን ድርጅቶችን፣ የሕንድ ኤምባሲንና በተለያዩ ጉዳዮች የተባበሩንን ሁሉ በራሴ፣ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲና በተጠቃሚዎች ስም በጣም አመሰግናለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ዩኒቨርሲቲያችን ከሕንድ የከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ተቋማት ጋር አጋርነት ለመመስረትና ለማጠናከር ፍላጐቱ መሆኑን እገልፃለሁ፡፡

የአገራችንን የ70 በመቶ ሳይንስና ቴክኖሎጂና የ30 በመቶ የህብረተሰብ ሳይንስ የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ በተገቢው ለማሳካትና የትምህርት ጥራትን ለማጐልበት ዩኒቨርሲቲያችን የቴክኖሎጂ ተቋም መሠረተ ልማት ማስፋፊያ አከናውኗል፡፡ ማስፋፍያውም የመማሪያ ክፍሎች፣ ቢሮዎች፣ ዎርክሾፖች፣ የተማሪዎች መኖሪያ ሕንፃዎችንና መንገዶችን ያካተተ ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲያችን የቴክኖሎጂ ተቋም 10 የቅድመ-ምረቃ የምህንድስና የስልጠና መስኮች፣ 9 የድህረ-ምረቃ የምህንድስና የስልጠና መስኮችን ትምህርት በማስተማር 40 በመቶ የዩኒቨርሲቲውን መደበኛ ተማሪዎችን እያገለገለ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ የተገነባው መሠረተ ልማት የዩኒቨርሲቲያችን የቴክኖሎጂ ትምህርት የበለጠ ተግባር ተኮር እንዲሆንና ለመማር-ማስተማር የተመቻቸና የተሳለጠ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ተቋሙንም የሐረማያ ቴክኖሎጂ ተቋም ተብሎ እንዲሰየም ዩኒቨርሲቲው ወስኖአል፡፡ ይህም መሠረተ-ልማት ማስፋፍያ በተጓዳኝ ዛሬ ስለሚመረቅ ክቡራን እንግዶች እንድትመርቁልንና ተቋሙን እንድትጐበኙ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡

በድጋሜ እንኳን ደህና መጣችሁ !

አመሰግናለሁ !

 

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ንግግር

$
0
0

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲና ህንድ አገር ከሚገኝ ቢ ኤም ቪ ኤስ ኤስ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች ለሚገኙ 300 አካል ጉዳተኞች የሰው ሰራሽ እግር ተከላና የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የመሰረት ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ምረቃ ላይ የተደረገ ንግግር


የተከበራቸሁ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤

የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ፤

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አካላትና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች እንኳን ደህና መጣችሁ! እንደምን ቆያችሁ!

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከምትገኝበት የኢኮኖሚ ደረጃ ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ መንግስታችን ዘርፈ ብዙ ዕቅዶችን በመንደፍና በመተግበር ተጨባጭ የሆነ ዕድገት እያስመዘገበ ይገኛል፡፡ እየተመዘገበ ያለውን ዕድገት በዘላቂነት እንዲቀጥል ለማስቻል፤ የ2ኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን በማዘጋጀትና በመተግበር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገም ይገኛል፡፡ ይህ ዕቅድ የሁሉንም ዜጎች እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችል ሁኔታ የተዘጋጀ ሲሆን አፈፃፀሙም ይህንኑ መሰረት አድርጎ እየተተገበረ ይገኛል፡፡

በዚህም በዕቅዱ የማህበራዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ ለአካል ጉዳተኞች፣ አረጋዊያንና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን የዴሞክራሲያዊና እና ሰብአዊ መብቶች እኩል ጥበቃ ለማድረግ እና በልማቱ  እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል  ከአገሪቱ ህገመንግስት ጀምሮ በበርካታ የዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና አገራዊ ህጎች ተረጋግጦ ለተግባራዊነቱም መንግስት ከአያሌ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁን የተደረገው ጥረት በሚፈለገው ደረጃ ያልደረሰ ቢሆንም፤ የአገራችን ዜጎች ብሎም የአካል ጉዳተኞች የትሩፋቱ ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል፡፡ የሚፈለገውን ዉጤት ለማግኘትና የዜጎችን በተለይም የአካል ጉዳተኞችን የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት ሽፋን ለማሳደግ የሚረዱ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ መንግሰት የአካል ጉዳተኞችን የአካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበትንም ዕቅድ በመተግበር የአካል ጉዳተኞችን ችግር ለማቃለል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀስቀስ ላይ ይገኛል፡፡የአካል ጉዳተኞችንም ችግር ለማቃለል መንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠት በሁሉም ክልሎች ውስጥ የአካል ጉዳተኞችን ችግር የሚከታተልና መፍትሄ የሚሰጥ እንዲሁም የተለያዩ ድጋፎችን የሚያሰባስብ መዋቅር እንዲዘረጋ አድርጓል፡፡

 

የአካል ጉዳተኝነት በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ሊከሰት የሚችል በመሆኑ፤ ኀብረተሠባችንን ባሳተፈ መልኩ በሰው ሰራሽ አደጋዎች የሚከሰቱ የአካል ጉዳተኝነት ለመቀነስና በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚደርሱ የተለያዩ ተፅዕኖዎችን ለመቀነስ መንግስት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራዎችንና የተለያዩ ድጋፎችንም በተለያዩ አካባቢዎች በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገኙባቸው አካባቢዎች በተለያዩ ዘርፎች የማኀበረሰብ አገልግሎት መስጠት ከተልዕኳቸው አንዱ በመሆኑ የአካል ጉዳተኞችን ችግሮች በማቃለል ረገድ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በፊት በአገራችን አካል ጉዳተኞች የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው የመማር እድል ያገኙ የነበሩት በጣም ጥቂት ሲሆኑ ይህንንም አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው በአንድ ዩኒቨርሲቲ ብቻ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ባለፉት አስር ዓመታት መንግስታችን የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሲባል በሰጠው ልዩ ትኩረት በበርካታ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አካል ጉዳተኞች የትምህርት እድል እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲም የአካል ጉዳተኞችን የትምህርት መብት ለማረጋገጥ የሚረዱ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ለአብነትም ያህል ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የመማሪያ ክፍሎች፣ የመኖሪያ ቤቶች እና እንዲሁም ልዩ የማንበብያ ክፍሎችና ቁሳቁሶችን በማሟላት ትምህርታቸውን በአግባቡ ተከታትለው በቂ እውቀት ጨብጠው እንዲወጡ ከፈተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

እነሆ ዛሬ እዚህ የተሰባሰብንበትም ዋነኛ ምክንያት የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በህንድ አገር የሚገኘውን ቢ.ኤም.ቪ.ኤስ ኤስ ከሚባለው ድርጅት ጋር የሥራ ትስስር በመፍጠር በምስራቅ አትዮጵያ አጎራባች ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ ከ270 እስከ 300 የአካል ጉዳተኞች ሰው ሰራሽ እግር ሰርቶ በመግጠም ለመንቀሳቀስ እንዲችሉ በማድረግ የአካል ጉዳተኛ ለሆኑ ወገኖቻችን እያደረገ ያለውን ድጋፍ ለማበረታት ነው ፡፡ ስለሆነም ይህ ጅምርና ተመሳሳይ የማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል ለሀረማያ ዩኒቨርሲቲ አደራ እላለሁ፡፡

መንግስት የተፈጥሮ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት እንዲስፋፋ ለማድግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲም በዚሁ የትኩረት አቅጣጫ መሠረት መንግስት ያስቀመጠውን ግብ ከማሳካት አኳያ አበረታች ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል፡፡ የዉጤቱ አንዱ ማሳያ የሆነውን የሐረማያ ቴክኖሎጂ እንስቲቲዪት መመረቁን በዚሁ እለት በይፋ አበስራለሁ፡፡

ክብራትና ክቡራን

በሀገራችን አንጋፋ ከሆኑት ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የሆነው የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ገንዘብ ከፍለው ጠበቃ ማቆም ለማይችሉ ሴቶች፣ ህፃናት፣ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች በየዓመቱ  እስከ 100 ሺህ ሰዎች ነፃ የህግ አገልግሎት በ43 ማዕከላት እና በሁለት የማህበረሰብ ተኮር የትምህርት ማዕከላት መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው በማድረግ፤ በአካባቢው የሚገኙ የጤና ተቋማትን የህክምና መስጫ ቁሳቁሶችን በማሟላት፤ በትምህርት ቤቶች የሚያስፈልጉ የትምህርት መረጃ ቁሳቁሶችን በማሟላት እንዲሁም በግብርና ፣ በስራ ፈጠራና ሌሎች ዘርፎች ጠንካራ ሥራዎችን በመስራት የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የዕውቀት ማዕከል በመሆኑ በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ዕውቀቶች የአካባቢውንና የሀገራችን ዜጎችን መጥቀምና በህይወታቸው ላይ ለውጥ እንዲመዘገብ የሚያስችል በመሆኑ የዛሬውን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን እየቀረፁ በሚተገብሯቸው ፕሮጀክቶች ለወገኖቻችን የጎላ ጠቀሜታ ላስገኙ ምሁራን ምስጋናዬን እያቀረብኩ ለወደፊቱም በተጠናከረና ከአጎራባች ክልሎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያለው ዕውቀት የዜጎችን ህይወት ለመለወጥ እንዲችል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የመንግስት ፍላጎት መሆኑን እየገለፅኩ መንግስትም የምታደርጉትን የጋራ የትብብር ሥራዎች የሚደግፍ መሆኑን ላረጋግጣላችሁ እወዳለሁ፡፡

ክቡራን የበዓሉ ታዳሚዎች

መንግስት ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘው የዕድገትና ትራስፎርሜሽን ዕቅድ ሲጠናቀቅ በአሁኑ ወቅት ያሉብን ማህበራዊ ችግሮች ጎልቶ በሚታይ ደረጃ የሚቀረፉ በመሆናቸው ፤ይህን ዕውን ለማድረግ የሁሉን ኢትዮጵያዊ የጋራ ጥረት የሚጠይቅ በመሆኑ ባለን ዕውቀት፣ ሀብትና ጉልበት ተጠቅመን በርብርብ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ዕድገት ዕውን እንድናደርግ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቅርባለሁ፡፡

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ኮሌጅ ባልደረባ የሆኑት ህንዳዊ መምህር ፕሮፌሰር አር.ኤስ ባንሳል ከግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር ባደረጉት ግንኙነት መሠረት ቀደም ሲል በትግራይ ክልል ለ400 አካል ጉዳተኞች እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት በሀረሪ ክልል፣ በሶማሌ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖችና እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተደዳር ውስጥ ለሚገኙ ከ270 በላይ ወገኖቻችን ከህንድ ሀገር ድረስ መጥቶ የሰው ሰራሽ እግር በመስራት ድጋፍ ላደረገው ቢ.ኤም.ቪ.ኤስ.ኤስ እና የፋይናንስ ድጋፍ ላደረገለት የጄ.ኤም.ሲ ግብረሰናይ ድርጅቶች ምስጋናዬን እያቀረብኩ ለወደፊቱም ትብብራችሁ እንዳይለየን እጠይቃለሁ፡፡

በመጨረሻም በኢትዮጲያ የህንድ ኤምባሲ እና የኢትዮጲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ይህንን በጎ አድራጎት ሥራ ለዜጎቻችን ስለአመቻቹልን በራሴና በኢትዮጲያ መንግስት ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡

አመሰግናለሁ፡፡

Announcement and Call of Abstract

$
0
0

Haramaya University College of Law (together with other Colleges and development partners) through its Pastoralist Areas Resilience Improvement through Market Expansion(PRIME) Project has planned to organize an ‘International Conference on Enhancing Pastoralists’ Livelihood and Resilience through Market Expansion’ on March 10-11, 2017 at Haramaya University. This international conference aims to bring together relevant stakeholders (GOs, NGOs, researchers, businesses and community) that operate in pastoral contexts for discussing and sharing new scientific evidences, development approaches, deliberate on policy options, and share key lessons related to pastoralists. The program includes presentation of lead and scientific papers, panel discussion on development approaches and poster show on key lessons. Therefore, this is to invite you to submit original scientific research and to attend the conference. For further information refer the below attached document.

HU Inaugurates IoT Expansion Project

$
0
0

FDRE President H.E. Dr. Mulatu Teshome inaugurated Haramaya University’s Institute of Technology expansion project. The project had cost over 284 million Birr to be completed.
3
The expansion project is composed of workshops and six fully equiped laboratories that totally cost more than 211 million Birr, and a G+3 building with 24 classrooms, 62 offices and computer centers, as well as teachers’ and workers’ lounge with a cost of 73 million Birr.
At the ceremony, Dr. Mulatu said the Ethiopian Government has special interests to expand the technology and natural science education in order to attain the country’s development goal; and HU is working hard toward to accomplish that, and is getting encouraging results. “This inauguration,” said the President “could be seen as one of the results”.
4
HU President, Professor Chemeda Fininsa said the completion of the expansion project provides a large potential for the University and the Institute, and pervades the shortage of practical teaching labs and workshops.
IoT Scientific Director, Dr. Asfaw Kebede explained that the institute was established in 1997 E.C, and has graduated more than 4,300 students in engineering fields for the last 12 years with first degree. Currently, over 5500 students are enrolled from first to third degree levels in 10 fields of study.
Dr. Asfaw said that they are working to develop their human resources and to construct infrastructures; and besides the teaching learning process, they are working with stakeholders in different sectors. He added, “We are also contributing to the development of our country by producing skilled manpower and by conducting cutting-edge research activities together with stakeholders. For instance, with Awash Basin Authority, we are working on the Awash River silt accumulation and related problems”.
According to Dr Asfaw Kebede the inaugurated facilities will assist they produce well skilled engineers who could be the backbones of our country’s renaissance.


AFRICAN CENTER OF EXCELLENCE IN CLIMATE SMART AGRICULTURE AND BIODIVERSITY CONSERVATION VACANCY ANNOUNCEMENT

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት ሰጠ

$
0
0

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ዛሬ ጥር 20 ቀን 2009 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ባካሄደው ስብሰባ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ለዶ/ር ፍቃዱ በየነ በ Institutional and Resource Economics የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት እንዲሰጥ ያቀረበውን ሀሳብ አጸደቀ፡፡

ዶ/ር ፈቃዱ በየነ ቀነኢ በሚያዝያ 8 ቀን 1964 ዓ.ም ቡሪ በምትባል መንደር በጃርቴ ጃርደጋ ወረዳ ከአሊቦ ከተማ በ5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኝ ቦታ ተወለዱ፡፡ ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አሊቦ የትግል ፍሬ ትምህርት ቤት ተከታተሉ፡፡ ከዚያም የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሻምቡ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1978 ዓ.ም እስከ 1981 ዓ.ም ተከታትለዋል፡፡ በ1982 ዓ.ም የሐረማያ ግብርና ዩኒቨርሲቲ በመግባት ለአራት ዓመታት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በሐምሌ 1985 ዓ.ም በግብርና ምጣኔ ሀብት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ ከተመረቁ በኋላ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በረዳት ምሩቅነት በግብርና ሥርፀት ትምህርት ክፍል ውስጥ በታህሳስ 1986 ዓ.ም ተቀጠሩ፡፡ ተቋሙን ለአንድ ዓመት ተኩል ካገለገሉ በኋላ የሁለተኛ ዲግሪ ስኮላርሽፕ በማግኘት በኔዘርላንድ ሀገር ዋግኒንገን ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል እ.ኤ.አ. በ1997 ዓ.ም በሰኔ ወር በ Management of Agricultural Knowledge Systems የሁለተኛ ዲግሪአቸውን አግኝተዋል፡፡ ከኔዘርላንድ በመመለስ ተቋሙን ለአምስት ዓመት ተኩል ካገለገሉ በኋላ እ.ኤ.አ. በመስከረም 2003 ዓ.ም German Academic Exchange Service (DAAD) ከሚባለው ድርጅት ስኮላርሺፕ በማግኘት ጀርመን ሀገር በሚገኘው ሁምቦልት ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቦርልን የሶስተኛ ዲግሪያቸውን እ.ኤ.አ በጥር 2008 ዓ.ም በ Institutional and Resource Economics አግኝተዋል፡፡ Challenges and Options in Governing Common Property በሚል ርዕስ የምርምር ፅሁፋቸው አቅርበው በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል፡፡
IMG_0255
ዶ/ር ፈቃዱ በየነ የሦስተኛ ዲግሪያቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በመመለስ ከማስተማር ጎን ለጎን የተለያዩ የምርምር ስራዎችን ሠርተዋል፡፡ እነኝህም በ Sustainable land management, customary pastoral land administration, food security and land use systems, and nature resource-based conflict ናቸው፡፡ በተጨማሪም ከማስተማር ጎን ለጎን ከ40 በላይ የሁለተኛ ዲግሪ እና 6 የዶክትሬት ተማሪዎችን አማክረዋል፣ የምርምር ውጤታቸውንም በታዋቂ መፅሄቶች ላይ እንዲያሳትሙ አድርገዋል፡፡ ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች ፕሮፖዛሎችን በመፃፍ የምርምር ድጋፍ አግኝተዋል፡፡ ከዚህም መካከል International Foundation for Science, Dry lands Coordination Group, Center for International Governance Innovation and centre for World Food Studies ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የምርምር ውጤቶችም በዓለም አቀፍ መፅሄቶች ላይ ታትመዋል፡፡ ከምርምር ስራዎች ባሻገር ለተለያዩ ድርጅቶች የምክር አገልግሎቶችን አበርክተዋል፡፡ ዋና ዋናዎቹ አልያንስ ፎር ግሪን ሪቮልሽን (AGRA)፣ የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP)፣ ቴትራቴክ ኤ.አር.አር፣ የምስራቅና የደቡባዊ አፍሪካ የማህበራዊ ሳይንስ ምርምር ድርጅት (OSSREA)፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ-መንግስታት ድርጅት (IGAD) እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት (UNDP) ናቸው፡፡

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከማስተማር በተጨማሪ የአፍሪካ ምጣኔ ሐብት ምርምር ኮንሰርትዮም (AERC) በሚመራቸው የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ውስጥ Institutional and Behavioral Economics እና Environmental Economics የሚባሉ የትምህርት አይነቶች (ኮርስ) በማስተማር አገልግለዋል፡፡

ከፒ ኤች ዲ ትምህርት መልስ ተቋሙን ለአራት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ እ.ኤ.አ. በሐምሌ 2012 የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ዕድገት አግኝተዋል፡፡ ዶ/ር ፈቃዱ ያካበቱትን የማስተማር እና የምርምር ልምድ በመጠቀም ለተለያዩ ድርጅቶች በተፈጥሮ ሐብት እንክብካቤ፣ በተፋሰስ እንክብካቤ፣ በሥርዓተ-ፆታ፣ ግብርናና ተፈጥሮ ሐብት ግንኙነት እንዲሁም ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ጋር ተያይዘው በሚነሱ ግጭቶች መከላከል ጉዳዮች ላይ ስልጠናዎችን ሰጥተዋል፡፡ በዚህም ረገድ በኬንያ እና ታንዛኒያ ከ26 የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ መምህራን በOSSREA ድጋፍ ባዘጋጁት የስልጠና ማንዋል በመጠቀም ስልጠናዎችን ሰጥተዋል፡፡

ዶ/ር ፈቃዱ በየነ ከሰሩት የምርምር ሥራዎች እና ካማከሩት የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ጋር በመሆን በአጠቃላይ 46 (አርባ ስድስት) የምርምር ፅሁፎችን በታወቁ አለም አቀፍ ሳይንሳዊ መፅሄቶች ላይ አሳትመዋል፡፡ በተጨማሪም ሶስት የውይይት ወረቀቶች (Discussion Papers)፣ 1 የስልጠና ማንዋል እና 2 የመፅሐፍት ምዕራፎችን (Book Chapters) አሳትመዋል፡፡
16252251_1347172732006320_9212603053877373207_o
ዶ/ር ፈቃዱ በየነ በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በሶስት የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሠርተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2002 ዓ.ም እስከ 2003 ዓ.ም የግብርና ሥርፀት ትምህርት ክፍል ኃላፊ ፣ ከ2008 ዓ.ም እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ የአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር ተቋም በዳይሬክርነት ፣ ከዚያም ከሰኔ 2012 እስከ መጋቢት 2016 ድረስ የአስተዳደር እና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ተቋሙን አገልግለዋል፡፡

በዚህም መሰረት ዶ/ር ፈቃዱ በየነ ቀነኢ ያስመዘገቡትን ውጤት እና ለማህበረሰቡ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ከግምት በማስገባት የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት መርምሮ ባፀደቀው መሰረት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ በ Institutional and Resource Economics የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት ከጥር 20 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ሠጥቷቸዋል፡፡

 

Haramaya University Confers the Rank of Professorship

$
0
0

Dr. Fekadu Beyene was born on April 16, 1972 G.C. in a village called Buri, 5 km away from Alibo Town. He attended primary and secondary school at Alibo Yetigil Fire, located in Jarte Jardega Woreda, East Wollega Zone. He also attended high school education at Shambu Town between 1985/86 to 1988/89 G.C. Then, in 1989/90 he joined the then Haramaya University of Agriculture. He graduated from the University in August 1993 in Agricultural Economics. Soon after graduation he was employed as a graduate assistant in the Department of Agricultural Extension. After serving the university for one and half years, he obtained a scholarship to attend MSc training at Wageningen University in the Netherlands and received Master’s Degree in June 1997 in the field of Management of Agricultural Knowledge Systems. After his return from Wageningen, he has been teaching various courses in the College of Agriculture for five and half years. In September 2003, he obtained scholarship from the German Academic Exchange Service (DAAD) to pursue PhD study at Humboldt University of Berlin in Germany and received terminal degree in January 2008 in the field of Institutional and Resource Economics. The title of his dissertation research was “Challenges and Options in Governing Common Property: customary institutions among pastoralists and agro-pastoralists in Ethiopia” and graduated with a great distinction.
IMG_0255
Dr Fekadu has been teaching different courses and conducted research on different issues of pastoral systems including sustainable land management, customary pastoral land administration, food security and land use systems, climate change and pastoral adaptations and natural resource-based conflict. He also supervised over 40 Masters and 6 PhD students who worked on sustainable watershed management, collective action in forest management, the influence of settlement on rangeland ecosystems and livelihoods, the impact of climate change on fisheries, challenges in the management of wildlife sanctuaries and related conflicts between conservation interventions and local livelihoods. He has been encouraging postgraduate students to publish their work. Dr Fekadu has obtained research grants from the following organizations: International Foundation for Science, Drylands Coordination Groups, Centre for International Governance Innovation, and Centre for World Food Studies. A number of articles were published from these research activities. He provided a number of consultancy services for different organizations including Alliance for Green Revolution in Africa (AGRA), World Food Program (WFP), Tetra-Tech ARD, Organization for Social Science Research in Eastern and Southern Africa (OSSREA), IGAD and UNDP. As a visiting scholar, he also taught postgraduate courses (such as Institutional and Behavioural Economics as well as Environmental Economics) in the regional MSc Programs run by the African Economic Research Consortium (AERC).

After serving the university for four years as assistant professor, Dr Fekadu Beyene was promoted to the rank of Associate Professor in July 2012. In addition to teaching and research, he has participated in provision of training for practitioners working in various organizations on diverse topics such as natural resource conflict management, gender, agriculture and natural resources and participatory watershed management. He coordinated the implementation of a number of externally funded projects. As a result of his continued engagement in teaching and research, he has published 46 journal articles, 3 discussion papers, 1 training manual and 2 book chapters.

Dr Fekadu served Haramaya University in various leadership positions as a Department Head between 2002 and 2003, as a Director for the Institute of Pastoral and Agro-pastoral Studies between 2008 and May 2012 and as a Vice President for Administration and Student Affairs between June 2012 and March 2016.
16252251_1347172732006320_9212603053877373207_o
Considering his achievements and contributions to development of the society, Haramaya University’s Senate and Administrative Board have promoted him to the rank of full professor in Institutional and Resource Economics.

Internal Vacancy

How to apply to study for MSc and PhD Degrees In Climate Smart Agriculture and Biodiversity Conservation at Haramaya University.

አስደሳች ዜና ለድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

$
0
0

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ በ2009 የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት በመደበኛው ፕሮግራም በተወሰኑ መርሃ-ግብሮች አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ በሁለተኛ ዲግሪ (Master) ትምህርት ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ሀ/ በመደበኛው ፕሮግራም ትምህርት የሚሰጥባቸው የድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብሮች፡-  

  1.  በ College of Social Sciences and Humanities
  • Master of Arts in Gender and Development Studies
  • Master of Arts in Afan Oromo ( Afan Oromo Teaching; Afan Oromo Literature and Applied Linguistics )
  • Master of Arts in History and Heritage Management
  1.  በ College of Education and Behavioral Sciences
  • Master of Arts in Educational Leadership and Management
  • Master of Arts in Social Psychology
  • Master of Arts in Special Needs and Inclusive Education

 

ለ/ የመመዝገቢያ የጊዜ ገደብ

አመልካቾች እስከ የካቲት 10 ቀን 2009 ዓ/ም ድረስ በግንባር ወይም መረጃዎቻችሁን በፖስታሣ. ቁ.138 ድሬዳዋበመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ሐ/ የመግቢያ ፈተናው የሚሰጥበት ቦታና ቀን፣

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ቅጥር ግቢ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን የካቲት 13 ቀን 2009 ዓ/ም ጧት ከሁለት ሰዓት ተኩል ጀምሮ ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 0255 53 03 32 ወይም 0255 53 0109 በሥራ ሰዓትደውለው ይጠይቁን።

ዝርዝር መረጃዎችንበዩንቨርሲቲው ዌብ-ሳይት http://www.haramaya.edu.et ለይማግኘት ይቻላል፡፡

                 ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ

               የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት

College of Law Ranks Third in Second National Annual Moot Court Competition

$
0
0

1
Haramaya University’s College of Law students competed and ranked third in a sixteen team national moot court competition hosted by Wollo University and Law Schools Consortium. The annual national moot court competition is the biggest in the country involving all public law schools across the nation.
2
From the invited sixteen teams based on pre-submitted written memorial, 8 teams were selected for the final oral litigation. Haramaya’s team was comprised of two students: Firew Kasaye and Nardos Tadesse, and their coach Daniel Esubalew who prevailed in the memorial screening and semi-final.
3
The national moot court competition was held in the city of Desse from December 22-24. The subject matter of the competition was ‘Regulation of Large Scale Agricultural Investment’ that has involved current and delicate issues such as: human rights, environmental protection, economic development and foreign direct investment.
Their coach, Daniel said, “The team members, Firew and Nardos, managed this demanding extracurricular commitment despite having to juggle full course loads, preparing for the upcoming national exit exam, and their managerial involvement in different clubs of the University. I am of the opinion that College of Law is exceedingly proud of their commitment to excel in advocacy.”


Barruulee Sagalee Haramaayaa

How to apply to study for MSc and PhD Degrees In Climate Smart Agriculture and Biodiversity Conservation at Haramaya University.

አስደሳች ዜና ! ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

$
0
0

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በርቀት  ትምህርት መርሃ-ግብር በ2009 ዓ.ም

  1. በ Accounting & Finance
  2. በ  Economics
  3. በ Management
  4. በ Agri-Economics & Agribusiness Management
  5. በ Rural Development & Agricultural Extension
  6. በ Natural Resource Management እና
  7. በ Horticulture

የትምህርት ዘርፎች  በቅድመ ምረቃ(ዲግሪ) መርሃ-ግብርተማዎችን ተቀብሎ  ማሰተማር ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ማንኛውም አመልካች እስከ የካቲት 5 ቀን 2009 ዓ.ም በሥራ ሰዓት  በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ ግቢ የርቀት ትምህርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርቦ ማመልከት የሚችል መሆኑን በደስታ እንገልጻለን፡፡

አመልካቾች-

  1. የቀድሞ 12 ኛ ወይም የ10ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና  ዉጤት እንግሊዘኛ እና ሂሳብን ጨምሮ 2.00   ነጥብና   ከዚያ በላይ ያላት/ያለዉ:: በተጨማሪም ዕዉቅና ካለው ዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ ዲፕሎማና  Level 4  የብቃት ማረጋገጫ ፈተና / COC/ ያለፈ/ች፡፡ ከዚያም  በላይ ያላት/ያለዉ፡፡
  2. የመሰናዶ  ትምርት ላጠናቃቁ አመልካቾች በየዓመቱ ት/ት ሚኒስቴር  ባወጣው በተከታታይና ርቀት ት/ት የከፍተኛ   ት/ት  መግቢያ  ዉጤት መሰረት ይሆናል፡፡

  ማሳሰቢያ፡-

  • ሁሉም አመልካቾች ዋናውን የትምህርት ማስረጃ ከማይመለስ ሁለት ፎቶኪፒ ና ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ጋር ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል
  • የማመልከቻፎርሙን ከርቀት ትምህርት ማስተባበሪያ ቢሮ ወይም  ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዌብሳይት (www.haramaya.edu.et/college of continuing and distance education )ላይ ማግኘት የምትችሉ ማሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ  ፡-0255530372/0255530096  ደውለዉ ይጠይቁን።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ     የተከታታይ እና  ርቀት ትምህርት  ዳይሬክቶሬት

Oduu Gamachisaa Wareen Barumsa barbaadan Hundaaf

$
0
0

Yuunvarsiitiin Haramaayaa sagantaa barnoota fagoottin bara baruumsaa 2009tti gosa barnootaa

  1. Accounting and Finance
  2. Econometrics
  3. Management
  4. Agri-Economics and Agribusiness Management
  5. Rural Development And Agricultural Extension
  6. Natural Resource Management fi
  7. Horticulture tiin barattoota digrii jalqabaatiin barsiisuu barbaada. Kanaafuu, kanneen barachuu barbaaddan marti  hanga Gurrandhala 5, 2009tii yeroo hojitti moraa Yuunvarsiitii Haramaayaa keessatti waajjira barnoota fagootti dhihaattani galmaahuu kan danddessan tahuu gamachuun isinii ibsina.

Iyyatoonni

  1. Warrii kutaa 12ffaa durii fi  kutaa 10ffaa ammaa xumurtan gosa barnootaa Herreegaa fi Ingiliffaa dabalate qabxii 2.00 fi sanii ol qabaachuu qabdan. Dabalataanis Yuunvarsiitii beekkamtii qabu irra  Dippiloomaa Koolleejji fi qormaata gahuumsaa (COC) sadarkaa  4ffaa (Levili 4) kan barban ta’u qaba.
  2. Sagantaa qophaa’inaa warra hordofaniif ulaagaa Minsteerri barnootaa bara baraan barnoota ol’anaa galchuuf baasu kan guutan ta’uu qaba.  

Hubachisa

  1. Iyyataan waraqaa ragaa orijinaali fi koppii lama lama suuraa lama waliin  qabatanii dhihaachuu qabu.
  2. Unkaa iyyannoo websaayitii Yuunvarsiitii Haramaayaa (www.haramaya.edu.et) irraa yookaan mooraa Yuunvarsiitii Haramaayaa keessatti waajjira Barnoota Fagoo irraa argachuu  dandeessan.

 

Yunivarsitii Haramayaa

Daayirektoreetti  Itti fufiinsaa fi Barnoota Faggo

MSc Thesis Research Grant for 2017 budget year Call for concept note: ISSD MSc grant

Viewing all 1085 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>